wisdom
እግዚአብሔር የመንገዱ መጀመሪያ አደረገኝ፥ በቀድሞ ሥራው መጀመሪያ።
መጽሐፈ ምሳሌ 8 : 22
ወዳጁን የሚንቅ እርሱ አእምሮ የጐደለው ነው፤ አስተዋይ ግን ዝም ይላል።
መጽሐፈ ምሳሌ 11 : 12
ጥበብን የሚያገኝ ሰው ምስጉን ነው፥ ማስተዋልንም ገንዘቡ የሚያደርግ፤
መጽሐፈ ምሳሌ 3 : 13
አትተዋት፥ ትደግፍህማለች፤ ውደዳት፥ ትጠብቅህማለች።
መጽሐፈ ምሳሌ 4 : 6
ወደ ዘለፋዬ ተመለሱ፤ እነሆ፥ መንፈሴን አፈስስላችኋለሁ፤ ቃሌን አስተምራችኋለሁ።
መጽሐፈ ምሳሌ 1 : 23
የዚያን ጊዜ ይጠሩኛል፥ እኔ ግን አልመልስም፤ ተግተው ይሹኛል፥ ነገር ግን አያገኙኝም።
መጽሐፈ ምሳሌ 1 : 28
ዘመንህ በእኔ ይበዛልና፥ የሕይወትህም ዕድሜ ይጨመርልሃልና።
መጽሐፈ ምሳሌ 9 : 11
ጥበብ ከቀይ ዕንቍ ትበልጣለችና የከበረ ነገር ሁሉ አይተካከላትም።
መጽሐፈ ምሳሌ 8 : 11
ከፍ ከፍ አድርጋት፥ እርስዋም ከፍ ከፍ ታደርግሃለች፤ ብታቅፋትም ታከብርሃለች።
መጽሐፈ ምሳሌ 4 : 8
እኔ ጥበብ በብልሃት ተቀምጫለሁ፥ እውቀትንም ጥንቃቄንም አግኝቻለሁ።
መጽሐፈ ምሳሌ 8 : 12

